የጎፈሬ ውድድሮች

Goferé Competitions

እስከመጪው የዓድዋ ድል በዓል (የካቲት 23፤ 2011 ዓ.ም.) ድረስ በጎፈሬ ድረገፅ፣ በኢንስታግራምና ፌስቡክ የተለያዩ ውድድሮች የሚካሄዱ ይሆናል። ከምንጀምራቸው ውድድሮች ውስጥ፤

 1. የሕዝብ ምርጫ ጎፈሬ (ከፍተኛ ድምፅ በማግኘት)
 2. ረጅም ጎፈሬ (የጎፈሬ ርዝመት በሜትር በመለካት)
 3. ጥበባዊ ጎፈሬ (ባላት/ ባለው ጥበባዊ አቀራረብ)
 4. ምርጥ የጎፈሬ ቪዲዮ
 5. አስቂኝ ጎፈሬ
 6. ባለምርጥ መልዕክት ጎፈሬ
 7. ሸላዩ ጎፈሬ (በሽለላና ቀረርቶ የሚያሸንፍ ጎፈሬ)
 8. የጎፈሬ ሞዴል

በአሁኑ ሰዓት በፌስቡክ ላይ ያለው “የሕዝብ ምርጫ ጎፈሬ” ውድድር ተጀምሯል። ተጨማሪ የውድድር ዘርፎች በቅርቡ የሚጀመሩ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች አሸናፊዎች የሚመረጡ ይሆናል። ውድድሮቻችን እንደየአይነታቸው በሕዝብ ድምፅ ወይም የጎፈሬ ፕሮጀክት በሚሰይማቸው ባለሙያ ዳኞች የሚዳኙ ይሆናል። ስለሆነም የሕዝብ ምርጫ አሸናፊነት እንዳለ ሁሉ የዳኞች ምርጫም ስላለ አዳዲስ ተወዳዳሪዎች ብዙ ተቀድመናል ብላችሁ ከመወዳደር ሳትዘናጉ ቀሪዎቹን ከ30 በላይ ቀናት እንድትጠቀሙና ድረ ገፃችንን በመጎብኘት አዳዲስ የሚጀመሩ ውድድሮችን በንቃት እንድትጠባበቁ እያሳሰብን፤ አያይዘንም ጥሩ ድምፅ ለማግኘት የሚረዱ ጉርሻዎች እግረ መንገዳችንን ልንጠቁማችሁ እንወዳለን።

 • የተለየ ፎቶግራፍ መነሳት (የፎቶግራፉ ሳቢነት፣ የተነሳበት ቦታ...)
 • የመወዳደሪያ ሊንካችሁን ለጓደኞቻችሁ ማጋራትና እንዲመርጧችሁ መጠየቅ፤ አልፎ አልፎም በትህትና ሳታሰለቹ ማስታወስ
 • የኢሜል አድራሻ የሚጠይቁ ውድድሮች ላይ ሂደቱ አሰልቺ ቢመስልም ኢሜል ማረጋገጥ የሚጠየቀው አንዴ ብቻ ነው ከዚያ በኋላ አይጠየቅም፤ ይህንን ለወዳጆቻችሁ ማሳወቅ፤ 
 • በውድድር 1 አንድ ሰው ለፈለገው ሰው በቀን አንዴ መምረጥ ይችላል፤ ስለሆነም ከአንድ ሰው ብቻ በቀሪዎቹ ቀናት ከ30 በላይ ድምፆችን ማግኘት ይቻላል። ሌሎች ውድድሮች የተለየ መሥፈርት ስለሚኖራቸው የጎፈሬ ድረ ገፅ ላይ የሚወጡ መረጃዎችን መከታተልና ግር ያለዎት ነገር ካለ በፌስቡክ ገፃችን ኢንቦክስ በማድረግ መጠየቅ፤ 
 • ከፎቶግራፍዎ ባሻገር የሚያስተላልፉትም መልዕክት ዋጋ ይኖረዋል
 • በማሕበራዊ ድረ ገፆች ላይ ያለዎትን ተሳትፎ መጨመር
 • ሁልጊዜ ከጎፈሬ ጋር የተያያዙ ፎቶዎችንና ሌሎች መረጃዎችን ሲያስተላልፉ #ጎፈሬነኝ ወይም #iamgofere የሚሉትን ሃሽታጎች መጠቀምና ወደፊትም የሚገለፁ ሌሎች ሂደቶችን መከተል የማሸነፍ ዕድልዎን ሊያሰፉልዎች ይችላሉ።

ጎፈሬ የፎቶ ውድድር ፩

Goferé Photo Competition 1

ማነው ጎፈሬ? ማናት ጎፈሬ?

Who's Goferé?

Gofere Logo with Pictures 01

ጎፈሬነት በተለይም ለጥቁር ሕዝቦች የተሰጠ የተፈጥሮ ስጦታ ሲሆን በታሪካችን የተለያዩ ጎፈሬዎችን ለማየት ችለናል። ጎፈሬ የወራሪ ጣልያንን ጦር የመከተ ነው፤ ጎፈሬ የራሱ ሃገር ነፃነት ብቻ ሳያንደላቅቀው ለሌሎች ነፃነትና እኩልነት በመላው ዓለም የተዋደቀና የተሰዋ ነው (የኮሪያ ዘማቾች፣ የኮንጎ ዘማቾች...)፤ ጎፈሬ የነጮችን የበላይነትን ተቃውማ የመከራ ገፈትን የቀመሰች ብላም ነፃነቷን ያስከበረች ነች (የአሜሪካ ሲቪል ራይት እንቅስቃሴ፣ አፓርታይድ)፤ ጎፈሬ በዝባዥ የፊውዳል ሥርዓትን ገርስሳ ለመጣል ቆርጣ የተነሳች ነች (በኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት የተማሪዎች ንቅናቄ)፤ ጎፈሬ አምባገነን ወታደራዊ ሥርዓትን የተቃወመ ብሎም የገረሠሠ ነው (የኢሕአፓ፣ የኢህአዴግ... የነፃነት ታጋዮች)፤ ጎፈሬ “አጭር ፀጉር መቆረጥ ጨዋነት ነው” የሚል ብሂል ስላልተዋጠለት ነፃነቱን መርጦ ፀጉሩን ለማጎፈር የደፈረ ነው (አርቲስቶች፣ ሙዚቀኞች...)፤ የተለያዩ ጎፈሬዎች አሉ... እነዚህ ጎፈሬዎች በዘር፣ በኃይማኖት ወይም በፖለቲካ አመለካከት ቢለያዩም ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ግን ለነፃነታቸውና ለማንነታቸው ያላቸው ጥልቅ ፍቅር ነው።

Goferé is an Amharic word that translates to “big hair,” close to meaning of the word “afro hair.”

The world has seen different versions of Goferés: those who fought colonizers; Goferés were not satisfied with their own freedom but rather fought and sacrificed their lives for the liberty of others all over the world; Goferés are those who fought the idea of one race being superior and another being inferior; Goferés fought feudal governments to bring about equality among all citizens; Goferés struggled to bring down dictators of all kinds; Goferés in their light form are persons that rebel from “clean cuts” to express themselves despite criticisms by their societies… Goferés come in many forms, but what connects them is their pursuit for freedom.

ከጎፈሬ ማሕበራዊ ድረ ገፆች

Recent Posts from our Social Media

Üsmäņ Jŕ added a new photo to Gofere's timeline.
kete nehe ke Eitopa nege Habhe
፸፰ኛው የድል በዓል አከባበር (78th Victory Celebration) የ፸፰ኛው የድል በዓል አከባበር በአራት ኪሎ የድል ሐውልት ዙሪያ ተከብሯል።
Gofere added 14 new photos.
እንኳን ለ፸፰ኛው የድል በዓላችን በሰላም አደረሳችሁ!
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
የዘንባባ ቀለበት አሰራር 2 - የአበባ ቀለበት - ምናለሽ እንኳን ለሆሳዕና በዓል አደረሳችሁ! የአበባ ዘንባባ ቀለበት አሰራር
እንኳን ወደ ምናለሽ በደህና መጡ! በቻናላችን ላይ የተለያዩ ጠቃሚና አዝናኝ ቪዲዮዎችን የምንለጥፍ ሲሆን ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግና ማሕበራዊ ድረ ገፆቻንን በመከተል ቤተሰብ .....
Making a Ring for Palm Sunday እንኳን ለሆሳዕና በዓል አደረሳችሁ! የዘንባባ ቀለበት አሰራርን ከእህት ገፃችን ምናለሽ ጋብዘናችኋል።
In this video we show you how you can easily create a pyramid ring for Palm Sunday. If you like this video please subscribe to our channel so that ...
Wedeb Newborn added a new photo to Gofere's timeline.
Tewodros Zeleke added a new photo to Gofere's timeline.
Tewodros Zeleke added a new photo to Gofere's timeline.
Hawi Reta added a new photo to Gofere's timeline.
Hawi Reta added a new photo to Gofere's timeline.
Tsega Kefyalew added a new photo to Gofere's timeline.
Getachew Tiruneh Schweiger added a new photo to Gofere's timeline.
ጎፈሬ
Gofere
Bezabehi Shawull added a new photo to Gofere's timeline.
Photos from Berekt Beyene's post Berekt Beyene added 3 new photos to Gofere's timeline.
hand holding tobacco pipe hand holding tobacco pipe 0 Repin Likes
Angela Davis Angela Davis 0 Repin Likes
One of my heroes, Angela Davis. One of my heroes, Angela Davis. 0 Repin Likes
cabelo-colorido-roxo-3 cabelo-colorido-roxo-3 0 Repin Likes
This Stunning Photo Series Celebrates Natural Hair In The Coolest Way And It's Empowering This Stunning Photo Series Celebrates Natural Hair In The Coolest Way And It's Empowering 0 Repin Likes
Natural Afro Hairstyles for Black Women To Wear Natural Afro Hairstyles for Black Women To Wear 0 Repin Likes
What a Huge Fro...Oh My... What a Huge Fro...Oh My... 0 Repin Likes
haircuts for black men with curly hair kinky braids afro haircuts for black men with curly hair kinky braids afro 0 Repin Likes